ወ/ሮ ይመኝ ጌቱ ይባላሉ።የደቡብ ጎንደር ሙጃ ሮቢት ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ የ41 ዓመት እድሜ እና የአራት ልጆች እናት ናቸው። ባለቤታችው ካረፉ ሰነባብቷል። የመጨረሻ ልጇ ሶስት አመቷን ከደፈነች ገና ወራትን እንኳ አልሳለፈችም። ከአንድ ዓመት በፊት የተለየ ሕመም ይሰማት ጀመር። ወደ አቅራቢያቸው ወዳለ የሕክምና ተቋም ሲትሄድ ሪፈር ብለዋት ወደ ተሻለ የሕክምና ተቋም ተላከች። በዚህ ግዜ የሀገሩ ሰው አዋጥቶላት…
